This support provides a tremendous boost to these families, helping them restore their health and eliminate the financial strain associated with purchasing cigarettes. Above all, it is a crucial step toward creating a clean, healthy, and peaceful environment—free from cigarette smoke—for the children they are raising in their homes.
All 17 recipients who received the support today have started their treatment with high morale and readiness, after receiving the necessary health counseling and usage instructions from our professionals.
This support will continue in the coming days.
A Word of Gratitude
This great achievement was made possible through the dedication of the European Abizer Family, who prioritized the health of our citizens and the well-being of our children by purchasing this expensive medication at their own expense and sending it from Europe. On behalf of our organization and the beneficiary families, we extend our highest gratitude for your unparalleled, life-saving support.
Let us continue to work together to achieve our vision of saving 1,000 lives!
Abizer – For a Better Community!
ዛሬ ለ17 ወገኖቻችን የሲጋራ ሱስ ማቆሚያ ድጋፍ አደረግን!
አቢዘር ማህበረሰብ አቀፍ የልማት ድርጅት (ACDO) በቅርቡ ይፋ ያደረገውን “የሲጋራ ሱስ ማገገሚያ ዘመቻ” አካል በማድረግ፣ ዛሬ ለሁለተኛ ዙር ከባቲ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር 17 ለሚሆኑ የቤተሰቦች አስተዳደሪዎች የኒኮቲን ምትክ ሕክምና (Nicotinell) መድኃኒቶችን በነፃ አከፋፍሏል። ይህ ድጋፍ እነዚህ ቤተሰቦች ጤናቸውን እንዲመልሱ እና ከሲጋራ ግዢ ጋር ተያይዞ ሲደርስባቸው የነበረውን የኢኮኖሚ ብክነት እንዲያስቀሩ ትልቅ አቅም የሚሰጥ ነው። ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ በየቤታቸው ለሚያሳድጓቸው ህፃናት ልጆቻቸው ቤተሰቦቻቸው ከሲጋራ ጢስ ነፃ የሆነ ንጹህ፣ ጤናማ እና ሰላማዊ አካባቢ ለመፍጠር የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ ነው። በዛሬው ዕለት ድጋፉን የወሰዱት 17ቱም ወገኖቻችን፣ አስፈላጊውን የጤና ምክርና የአጠቃቀም መመሪያ ከባለሙያዎቻችን አግኝተው ሕክምናቸውን በከፍተኛ የሞራል ዝግጁነት ጀምረዋል። ይህ ድጋፍ በቀጣይ ቀናትም ይቀጥላል። ይህ ታላቅ ተግባር እውን ሊሆን የቻለው፣ የወገኖቻችሁን ጤና እና የልጆችን ደህንነት አስቀድማችሁ ይህንን ውድ መድኃኒት በራሳችሁ ወጪ ገዝታችሁ ከአውሮፓ ለላካችሁልን የአውሮፓ የአቢዘር ቤተሰቦች ጥረት ነው። ላደረጋችሁት ወደር የለሽ የሕይወት አድን ድጋፍ በድርጅታችን፣ እና በተጠቃሚ ቤተሰቦች ስም የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን። የጀመርነውን 1,000 ሰዎችን የመታደግ ራዕይ ከዳር ለማድረስ የሁላችሁም ትብብር አይለየን!
አቢዘር – ለተሻለ ማህበረሰብ!










