አቢዘር (ACDO) በአዋሽ 7 ኪሎ ከተማ ከ400 ለሚልቁ ወላጆቻቸውን ያጡ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ አበረከተ

  • Home
  • Educations
  • አቢዘር (ACDO) በአዋሽ 7 ኪሎ ከተማ ከ400 ለሚልቁ ወላጆቻቸውን ያጡ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ አበረከተ

ከአዲስ አበባ እስከ አዋሽ የተዘረጋው የደግነት ብርሃን በአዋሽ 7 ኪሎ ከ400 ለሚልቁ የቲም ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ!
“አንድም የቲም ልጅ ወደ ኋላ አይቀርም ተስፋን በመላ ኢትዮጵያ!”
የአቢዘር ማህበረሰብ ልማት ድርጅት (ACDO) ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ (የቲም) ህፃናት በቁሳቁስ እጦት ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዳይስተጓጎሉና የነገ ተስፋቸው እንዲለመልም በማለም የጀመረው ሀገር አቀፍ የቅስቀሳና የድጋፍ ጉዞ ሁለተኛ መዳረሻውን በአዋሽ 7 ኪሎ ከተማ በደማቅ ሁኔታ አከናውኗል።
በዛሬው ዕለት በአዋሽ 7 ኪሎ ከተማ ለሚገኙ ከ400 ለሚልቁ የቲም ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ (ደብተሮች፣ እስክሪብቶዎችና እርሳሶች) በክብርና በደስታ ተበርክቷል።
🏛️ በክብር እንግዶች የታጀበው ይፋዊ የድጋፍ መርሃ-ግብር
ይህ የተቀደሰ የድጋፍ ስነ-ስርዓት የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት የተካሄደ ሲሆን፣ በመርሃ-ግብሩ ላይ፦
* ክቡር አቶ አብዱ አሊ — የአዋሽ ሰባት ከተማ ከንቲባ
* ወይዘሮ ፋጡማ ኡመር — የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
* ወይዘሮ አስያ ኡመር — የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
* አቶ ሀሰን ሁመድ — የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
በአካል ተገኝተው ለህፃናቱ ማበረታቻ የሰጡ ሲሆን፣ አቢዘር ለወገን ደራሽ በመሆን እያከናወነ ላለው አርአያነት ያለው ሀገራዊ የበጎ አድራጎት ስራ ያላቸውን ጥልቅ አድናቆትና አጋርነት ገልጸዋል።
የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ማህበረሰቡም እነዚህን ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት ከራሱ ልጆች እኩል አይቶ እንዲያስተምርና አለኝታ እንዲሆናቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
✨ የተስፋው ጉዞ ይቀጥላል!
በአዳማ ከተማ ለ400፣ ዛሬ ደግሞ በአዋሽ 7 ኪሎ ከ400 ለሚልቁ ተማሪዎች የተደረገው ድጋፍ ለጋስ እጆችና ደጋፊዎቻችን ከጎናችን በመቆማቸው የተገኘ የጋራ ድል ነው። የምስራቁ የሀገራችን ክፍል የደግነት ጉዟችን ወደ ቀጣዮቹ መዳረሻዎች በከፍተኛ ወኔ ይቀጥላል!/

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *