የደግነት ብርሃን በአዳማ 400 ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገላቸው

  • Home
  • Educations
  • የደግነት ብርሃን በአዳማ 400 ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገላቸው

ከአዲስ አበባ እስከ አዳማ የተዘረጋው የደግነት ብርሃን 400 የቲም ልጆች በትምህርት ተስፋ ፈኩ!
“አንድም የቲም ልጅ ከትምህርት ገበታ መቅረት የለበትም!”
የደግነትና የተስፋ ጉዟችን የመጀመሪያ ምዕራፍ በታላቅ ድልና በልጆች ያልጠፋ ፈገግታ ተጠናቋል!
ዛሬ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ከአቢዘር ዋና ቢሮ የተነሳው የልዑካን ቡድናችን፣ የመጀመሪያ መዳረሻው ባደረጋት በአዳማ ከተማ ለሚገኙ 400 ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ (የቲም) ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ በክብርና በደስታ አበርክቷል።
የልጆቹ ፊት ላይ የታየው ብሩህ ተስፋ፣ የእናቶች የእፎይታ እንባና ልባዊ ዱዓ የሁላችንንም የድካም ውጤት እጅግ ጣፋጭ አድርጎታል።
📌 የዛሬው ታላቅ የድጋፍ መርሃ-ግብር ድምቀቶች፦
* 400 አዳዲስ ተስፋዎች፦ የደብተር፣ የቦርሳና የሌሎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች እጦት በትምህርት ገበታቸው ላይ እንቅፋት እንዳይሆንባቸው ሙሉ ቁሳቁስ ተደራሽ ተደርጓል።
* የማህበረሰብ ንቅናቄ፦ በአዳማ ከተማ ማህበረሰቡ ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ልጆችን ከራሱ ልጆች እኩል አይቶ እንዲያስተምርና አለኝታ እንዲሆናቸው ጥሪ ቀርቧል።
* የጋራ ጥረት ውጤት፦ ይህ ስኬት ከጎናችን ለቆማችሁ ለጋስ እጆች፣ ሌት ተቀን ለደከሙ የአቢዘር ቤተሰቦችና በዱዓ ላገዛችሁን በሙሉ የተገኘ የጋራ ፍሬ ነው።
የምስራቁ የሀገራችን ክፍል የደግነት ጉዟችን ገና ጅማሮው ላይ ነው፤ ወደ ቀጣዮቹ ከተሞችም ጉዟችን በብርታት ይቀጥላል!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *